ሸበላው retweeted
የዕለቱ አንኳር ዜናዎች ህዳር 18/2019 ዓ.ም
1. ከአንድ ወር በላይ በከባድ ግጭት ውስጥ ባለፈችው ሞያሌ ፌዴራል ፖሊስ መሰማራቱን ተከትሎ፣ ግጭቱ መርገቡን ነዋሪዎች ለሆርን ፎሪኩዌንሲ ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት በተከማዋ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሰማርተው ሲዘዋወሩ መመልከታቸውን ጠቁመዋል። ግጭቱ ለጊዜው መቆሙን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ውስን የሰው እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።
2. የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ኡመር በክልሉ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ በልማት ፕሮጀክቶችና በጸጥታ ሁኔታው ዙሪያ እየተነሱ የሚገኙ ቅሬታዎች ሰላምና መረጋጋት ወደማናጋት እንዳያድጉ አሳሰቡ። ፕሬዝዳንቱ በይፋ ፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መልዕክት፣ የልማት ፕሮጀክቶችና የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ላይ ጥያቄ ማንሳት እና የክልሉን ሰላም ማደፍረስ መለየት እንደሚገባ ገልጸዋል። የሚነሱ ቅሬታዎች በሕጋዊና በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
3. የገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየቱን አስታውቋል። ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በዛሬው ስብሰባው በፓርቲው ስትራቴጂካዊ አጀንዳዎችና በልዩ ልዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ፓርቲው አስታውቋል። ምንም እንኳን ስብሰባው ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁ ቢገለጽም፣ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የተባለ ነገር የለም።
4. የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ሚፈቅደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ፣ አደጋ እንደሚያስከትል የዘርፉ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው። የውጭ ባንኮች 100 በመቶ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ከተደረገ፣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የጥገኝነት ስጋት እንደሚያስከትል ተጠቁሟል። ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮችን ከሰሞኑ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሙሉ ቁጥጥር እንዲኖራቸው የሚፈቅድ መመሪያ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።
ሸበላው retweeted
እነ ልጅ ኤርምያስ @mulugetaermias1 , ከሳምንታዊ YouTube (@HornFreqe on YouTube) ፕሮግራማቸው በተጨማሪ በየቀኑ 'አንኳር' ዜናዎችን በ @thehornfreqe እያስተላለፉ ነው::
በርቱልን::
@himaawol 'አበረታቻቸው' ለማለት ነው::
''ጥቅሜ ይቀጥላል '' በሚል ተነቦዋል። አማራ ሲተርት "የፈሩት ይደርሳል፣ የጠሉት ይወርሳል " ይላል
🇪🇹 ይህ መንግሥት ለረጅም ጊዜ ይቆያል። ባጭሩ፣ እንደ ቼዝ ግራንድማስተር ነው፤ ማሸነፍ ቀላል አይደለም። @AbiyAhmedAli
እሱ ቼዝ ይጫወታል፤ እናንተ ግን ዳማ እየተጫወታችሁ ነው። leadership
62
ሸበላው retweeted
የዕለቱ አንኳር ዜናዎች ህዳር 17/2019 ዓ.ም
1. ኢትዮጵያ በባህር በር ጉዳይ በኤርትራ ላይ ወረራ እንደማትፈጽም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው የፓርላማ ማብራሪያቸው፣ "ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ብላ ኤርትራን ልትወር ነው" ይባላል ያሉትን ስጋት አስተባብለዋል። የሚነሳውን ስጋት ውድቅ ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ወረራ አናካሂድም" በማለት የመንግሥታቸውን አቋም ይፋ አድርገዋል።
2. ኤርትራ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና በባህር በር ጉዳይ "የጦርነት ዛቻ ማስተጋባቱን" ካቆመ፣ ወደብን ጨምሮ ለጋራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች። የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ አስመራ ወደቦችን በጋራ ጥቅምና በኤርትራ ሉዓላዊነት መርህ ለኢትዮጵያ ክፍት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ሉዓላዊነትን ለሚጋፋ የኃይል ጫና እና የግዛት ማስፋፋት ዓላማ እንደማትተባበር መግለጫው ጠቁሟል።
3. የአፍሪካ ኅብረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሱዳን ኃይሎች ያቀረቡት የሰላም ጥሪ ተከትሎ፣ ባወጣው አቋም መግለጫ ሂደቱ በሱዳናዊያን መመራት አለበት ብሏል። በአዲስ አበባው የውይይት ጥሪ ድጋፍ የሰጠው ኅብረቱ፣ ማንኛውም የሰላም ጥረት በገለልተኝነት ሚና መከናወን አለበት ብሏል። ኅብረቱ የሱዳን ኃይሎች ለጥሪው የሰጡትን ምላሽ መመልከቱን የጠቆመ ሲሆን፣ በሱዳን ሉዓላዊነት ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳለው ገልጿል።
4. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ከተማ በረራ ነገ ህዳር 18/2019 ዓ.ም እንደሚጀመርም አስታውቋል። በጸጥታ ችግር ሁለት ወር ገደማ የተቋረጠው የአክሱም በረራ ዳግም የተጀመረው፣ ዓመታዊው አክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል ዋዜማ ነው። ለበዓሉ የበረራ አግልግሎት እንዲደርስ ታሳቢ ተደርጎ፣ ባለፉት ቀናት በአየር መንገዱ ዝግጅት ሲደረግ እንደነበር ተሰምቷል።
ሸበላው retweeted
#Ethiopia is nearing completion of its constitutional reform process, Prime Minister Abiy Ahmed told parliament, citing public recommendations gathered through the National Dialogue Commission.
hornfrequency.org/index.php/…
ሸበላው retweeted
🚨 LES CHRÉTIENS ÉTHIOPIENS SONT MASSACRÉS PENDANT QUE LE MONDE REGARDE AILLEURS.
Des archevêques orthodoxes éthiopiens appellent désormais les fidèles à s’organiser et à défendre leurs communautés face à une persécution qui s’aggrave.
Plus de 60 chrétiens orthodoxes tués en quelques jours dans la zone d’Arsi (Oromia) en octobre.
Des familles entières, des enfants, des églises attaquées.
Les attaques continuent.
Où est la protection de l’État ?
Où est la communauté internationale ?
Où sont les médias ?
Les Amhara et les chrétiens orthodoxes d’Éthiopie ne sont pas des vies jetables.
« Si un membre souffre, tous les membres souffrent avec lui. »
1 Corinthiens 12:26
Le silence n’est pas neutre. Il est complice.
#PrayForEthiopia #Amhara #EndChristianPersecution #EthiopianOrthodox #StopTheKillings
🤖 Made with AI
ሸበላው retweeted
Attacks targeting Christians across Europe surged 44% in 2025, with a new watchdog report documenting 2,465 anti-Christian hate crimes and incidents. France, England & Wales, Germany and Austria recorded the highest totals.
The Vienna-based Observatory on Intolerance and Discrimination Against Christians in Europe (OIDAC) says the sharpest concern is the rise in attacks targeting individuals, not just property. Clergy and people visibly associated with churches were the most frequently attacked, and that category saw the strongest increase.
A George Washington University extremism expert tells Fox News Digital that anti-Christian attacks often receive far less public attention than similar incidents targeting other faith groups, saying, "While the law might be neutral, the common perception of things is not neutral, and so those incidents are not prioritized."
See what some officials are now calling for in response to the findings: foxnews.com/world/christians…
ሸበላው retweeted
የዕለቱ አንኳር ዜናዎች ህዳር 16/2019 ዓ.ም
1. በኢትዮጵያ ጦር እና በኤርትራ ጦር እንዲሁም በሕወሓት ኃይሎች መካከል፣ በዛሬ ዕለት በባድመ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ውጊያ መካሄዱ ተሰምቷል። ውጊያ ገመሃሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተካሄደ መሆኑን የታወቀ ሲሆን፣ የድንበር ወታደራዊ ፍጥጫው ይበልጥ ማየሉን ከስፍራው የተገኙ መረጃዎች አመላክተዋል።
2. በጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን የሱዳን ኃይሎች ውይይት እንደማይቀበል አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን ጦርነት ሰላማዊ መፍትሔ የማመቻቸት ሚና ለመወጣት የሚያስችል የገለልትኝነት አቋም የለውም በሚል ነው። በአንጻሩ በጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ መቀበሉን አስታውቋል። ይሁን እንጂ በአዲስ አበባ በሚመቻቸው ውይይት ለመቀመጠ የመሰረተውን የሽግግር መንግሥት እውቅና መስጠትን እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።
3. በኢትዮጵያ ሙስና የደህንነት ስጋት እና የዜጎች ኑሮ ጫና ምንጭ መሆኑን የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን 23ኛውን የዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሙስና ከተደራጁ ወንጀሎች ጋር ሲመጋገብ፣ በሀገር ደህንነት፣ በኢኮኖሚና በዜጎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ገልጿል። ከፍተኛ ሙስና ከሚፈጸምባቸው ተቋማት መካከል ኢሚግሬሽን፣ ጉምሩክ፣ ፖሊስና ፍርድ ቤቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል።
4. በታሪክ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረው የኤችአይቪ ሥርጭት ከሚቀጥለው የአውሮፓውያኑ ዓመት ጀምሮ ሊጨምር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤችአይቪ ኤድስ ፕሮግራም አጠነቀቀ። በገንዘብ ድጋፍ እና በአገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት ዓለም በሽታውን ለማጥፋት ጫፍ ላይ በደረሰበት ወቅት የቫይረሱ ሥርጭት ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት ተደቅኗል ብሏል። በኢትዮጵያ የቫይረሱ መከላከልና ግንዛቤ ፈጠራ እንቅስቃሴ በመቀዛቀዙ፣ ስርጭት በአሳሳቢ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑን ሆርን ፎሪኩዌንሲ በጉዳዩ ላይ የዳሰሳ ጥናት ያደረጉ የጤና ባለሙያዎችን አነጋግሮ መዘገቡ ይታወሳል።
ሸበላው retweeted
Christians are being executed inside their own churches.
Worshippers are being burned alive, and young girls are being abducted, forced into marriage, and pressured to abandon their faith and convert to Islam.
A 2026 Open Doors report says:
- 388 MILLION Christians across the globe face high levels of persecution and discrimination.
- 4,849 Christians were killed for their faith.
- 3,632 churches and Christian properties were attacked or shut down.
This is what radical Islam does to the world. We cannot allow Sharia Law anywhere near our nation. May God protect us.
ሸበላው retweeted
Intelligence sources tell Horn Frequency that al-Shabab is reportedly plotting an attack targeting Ugandan troops withdrawing from Somalia’s Lower Shabelle region. The group is said to be mobilizing fighters from Hiiraan, raising concerns over the security implications of the ongoing troop withdrawals.
hornfrequency.org/index.php/…
ሸበላው retweeted
— 4,300 RSF fighters trained on #Ethiopian soil
— 187 drones from Ethiopia, 484 civilian casualties
— Khartoum bombed days before his peace call
Abiy Ahmed promises "equal distance" in Sudan. The record speaks for itself. A party to the war can't be its mediator.
barazabrief.com/2026/11/dron…
እነዚህ አውሮፕላኖች አስመራ ቢያርፋ የመሬት መንቀጥቀጥ ይነሳል
ሰበር!
7 ግዙፍ ራሺያ ስሪት የጭነት አውሮፕላኖች ትናንት #ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሰምተን ደስታችን ወሰን የለውም!
ከዝህ ጎን ለጎን፣ ኤርትራ ክፍለ ሐገር ስንት አውሮፕላን ነው ያላት?
ሸበላው retweeted
At least 14 #Amhara civilians were killed and more than 12 youths abducted during attacks attributed to #Oromia's Gadaa Commando forces in Limu Gelila, Horo Guduru Wollega.
Residents reported house-to-house searches across four villages, the discovery of nine bodies in abandoned homes and widespread displacement.
Displaced families face severe food shortages and a lack of humanitarian assistance.
ሸበላው retweeted
የዕለቱ አንኳር ዜናዎች ህዳር 14/2019 ዓ.ም
1. የሞያሌ ግጭት በፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት ለቀናት ከረገበ በኋላ ዳግም ተባብሶ ቀጥሏል። ትላንት ህዳር 13/2019 ዓ.ም ያገረሸው ግጭት በከባድ መሳሪያ ተደግፎ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሆርን ፍሪኩዌንሲ ተናግረዋል። መጠነ ሰፊ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እያከስከተለ የሚገኘውን ግጭት ለማስቆም፣ በሶማሊ እና ኦሮሞ ባለሥልጣናት መካከል ንግግር እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
2. በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ መሻሻሉን ባለአደራ አስተዳደሩ አስታውቋል። ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ማሻሻያ የሰው እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2:00 ድረስ የነበረው ወደ 4:00 የተሻሻለ ሲሆን፣ የባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2:00 ድረስ እንዲሆን መደረጉ ተገልጿል።
3. ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው የተባለ ድሮን በሱዳን ካሮቱም ከተማ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መገልገያ ህንፃ መምታቱ ውግዘት አስከትሏል። ምንም እንኳን የድሮኑ መነሻ ከኢትዮጵያ መሆኑ ባይረጋገጥም፣ በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የተፈጸመ መሆኑ ተገልጿል። ሱዳን የድሮኑ መነሻ ኢትዮጵያ ባህር ዳር መሆኑን በመግለጽ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለፈጥኖ ደራሹ ኃይል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ማረጋገጫ ነው ብላለች።
4. በቱርክ አስተናጋጅነት የተካሄደው ኮፕ 31 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ያለ ስምምነት መበተኑ ተሰምቷል። የተባበሩት መንግሥታት ኮፕ 31 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የተገኙ የዓለም አገራት በነዳጅ እና በፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶቸቻውን ማጥበብ ባለመቻላቸው፣ አየር ንብረት ለውጥን መከላከል የሚያስችል አዲስ ትልቅ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ተበትነዋል። ኢትዮጵያ ያለ ስምምነት የተበተነውን ጉባኤ በሚቀጥለው ዓመት ለማስተናገድ ተረክባለች።
ሸበላው retweeted
New footage from Bole International Airport in Addis Ababa, #Ethiopia, reportedly shows around seven UAE-linked Il-76TD cargo aircraft.
The aircraft have been linked to suspected weapons and ammunition shipments to Sudan's Rapid Support Forces (RSF), drawing renewed attention to the #UAE-Ethiopia air cargo network and its potential role in Sudan's ongoing war.
barazabrief.com/2026/11/uae-…





















