jony (@AdaneMitku) profile picture

FBI

Joined November 2021
Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)Photo by jony (@AdaneMitku)
እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በደህና አደረሳችሁ!! በያላችሁበት ምልካም የገና በዓል እመኛለሁ:: በዓል ስናከብር ይህ ዕድል የሌላቸውን: የተጎዱትን: የተፈናቀሉትን..ብዙሃን እያሰብን ብቻ ሳይሆን በዘላቂነት ለመደገፍ የምንነሳሳበት ይሁን::
35
4
610
20,851
ወሎ የአንድነት ድግስ ጀመረ!! ተጠባቂው የኮሎኔል ፈንታሁን መግለጫ.... የፋኖ መሪው ምላሽ ሰጠ!! ዝርዝሩን ... Haddis Media ላይ ያድምጡ:: ሊንክ......👇👇👇 youtu.be/8D2N5sDIapg?si=M957…
1
14
34
1,556
የአንካራውን ስምምነት መግለጫ ካነበብኩ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ የሚከተልውን መረዳት ችያለሁ። - በጋራ መግለጫው ላይ ባይገለጽም ኢትዮጲያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ሽራለች። ሶማሊያ ደግሞ የኢትዮጲያ ጦር ከሀገሯ እንዲወጣ ስታራምደው የነበረውን አቋም ቀይራለች። - ከሶማሊላንድ ጋር ተደርጎ የነበረው ስምምነት ኢትዮጵያ ሶማሌላንድን እንደ ነጻ ሀገር እውቆና ለመስጠት፤ በምትኩም ለወደብ እና የባህር ኃይል የሚሆን የባህር በር ማግኘት እንደነበር የሚታወስ ነው። የአንካራው ስምምነት ደግሞ ኢትዮጲያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር፣ ሶማሊያ ደግሞ ወደቦቿን ኢትዮጲያ እንድትጠቀም እንድትፈቅድ የሚል ነው። - ይህ ማለት የአንካራው ስምምነት ኢትዮጲያን የባህር ወደብ ባለቤትነት ሳይሆን የመጠቀም መብትን የሚወስን ነው። ማለትም የኢትዮጲያ መንግስት በሶማሊላንዱ ስምምነት ተጎነጻፍኩት ሲለው የነበረው የወደብ ባለቤትነት ቀርቶ፣ የሶማሊያንም ሆነ የሌላ ሀገራትን ወደብ በሊዝ፣ በኮንትራት ወዘት የሁለትዮሽ ስምምነት መጠቀም ትችላለች በሚለዉ ተተክቷል። ይህ ደግሞ እንደ United Nations Convention on the Law of the Sea (UNCLOS) ያሉ የአለም አቀፍ ህጎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ሶማሊያም ሆነች ሌሎች ጎረቤቶቻችን ድሮውንም የተቀበሉት ጉዳይ ነው።ለምሳሌ ጂቡቲ የታጁራን በሊዝ ለኢትዮጲያ ለመስጠት እንደምትፈልግ ደጋግማ ተናግራለች። ሲጠቃለል የአንካራው ስምምነት የኢትዮጲያ እና ሶማሊያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሁም ኢትዮጲያ የወደብ ባለቤት ለመሆን የምታደርገውን ሙከራ ከአምና (የሶማሊልንዱ ስምምነት ከተፈረመበት ከጃኑዋሪ 1፣ 2024) በፊት ወደነበረበት የሚመልስ ነው። ለዚሁ ነበር ያን ሁሉ ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ የተከፈለው? ሀገር የምትመራው በእውቀት ላይ በተመሰረተ የሰከነ እቅድ ይልቅ በባብዶ ምኞት ሲሆን ውጤቱ ሀገራዊ ተዓማኒነት (credibility) በእጅጉ መጉዳት ነው። በዚህ ጉዳይ ከተፈጸሙ ስህተቶች እና የደርሰውን ሀገራዊ ኪሳራ ለማመን እና ለመማር ዝግጁ የሆነ ዓዕምሮ ካለን፣ ወደፊት እንዳንደግመው ይረዳን ይሆናል።
389
239
58
1,414
175,282
የቀድሞ ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመቀንጨር ላይ የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያስመርቅ ተነግሯል። የአእምሮ መቀንጨር ለሚያሰቃየው የብልጽግናው መንደር የቅድሚያ ትኩረት እንዲሰጠው ቢደረግ ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለኝ። ከነቅሌቱ ከአንካራ ቱርክ የተመለሰውን የብልጽግናውን አለቃ ቀለም ለመቀባት በዚያ መንደር የሚደረገውን መንተፋተፍ ስመለከት ''አንድ ላይ ብንኖርም ተለያይተናል'' የሚለውን አባባል አስታወሰኝ። በእውነት አንድ ክፍለ ዓለም ላይ ነው ከብልጽግናው መንደር ነዋሪዎች ጋር አየርና ጸሃይ ተጋርተን የምንኖረው? ሰውዬው በራሱ አንደበት 'ህልሜን እንጂ የነገርኳችሁ መቼ በእኔ ዘመን የወደብ ባለቤት እንሆናለን - አልኩኝ?' ያለበትን ክሊፕ ቆርጬ የላኩለት አንድ ንዝንዝ ያደረገኝ የዚያ መንደር ነዋሪ ምን ብሎ መለሰልኝ መሰላችሁ? ''ቱርክ ላይ ህልሙን አሳክቶ ተመልሷል'' ከእንደዚህ ዓይነት ሰው ጋር እንዴት መግባባት ይቻላል? አቶ ደመቀ መኮንን የዚህን መንደር ነዋሪ ሰብስበህ የመቀንጨር ህክምና እንዲወስዱ በማድረግ ስራህን ብትጀምርልን ውለታህን ሀገር ትከፍልሃለች። ሰው በገዛ ፍቃዱ ደደብና እንጉልፋቶ ሲሆን ምን ማድረግ ይቻላል? አረ ፍሬን በጥሳችሁ ተያይዛችሁ ገደል እንዳትገቡ?! እውነት ለመናገር የብልጽግናን መርፌ ስትወጉ ህሊና የሚባለውን ትንሹን እግዚያብሄር ቆርጣችሁ እንደምትጥሉ ነው የተረዳሁት። ሰው በዚህ ደረጃ ሲደነቁር የታዘቡት እማማ ዝናሽ ''ስምንተኛው ሺህ ገብቷል'' ብለው ኡኡታቸውን ያስነኩበት ድምጻቸው ጆሮዬ ላይ ያቃጭልብኛል። በተለይ ''ሀገርና ፖለቲካን እንለይ'' የሚሉ አስመሳዮችን እንዴት እንደምጠየፋቸው?! ከእነዚህኞቹ አንደኛውን ጓዙን ጠቅልሎ፥ ሆዱን ሸክፎ ብልጽግና መንደር የገባው አለሌ በስንት ጣዕሙ?! በእነሱ ቤት ራሽናል መሆናቸው ነው። የሀገር ፍቅር ደማቸው ውስጥ እየተንተከተከ ተቸግረዋል። አሁን ማን ይሙት የአብይ አህመድን እብደት ሉጋም ይበጅለት ለሚለው የብዙሃን ጥያቄ ''ሀገርና ፖለቲካ እንለይ'' የምትል ክልሼ መሰንቀር ምን የሚሉት 'ራሽናል' አስተሳሰብ ነው? በህልምና በራዕይ፥ በቅዠትና በነባራዊ ሁኔታ መሃል ድንበሩን አጥፍቶ ሀገርን 'በደመነፍስና በጨበጣ' ካልመራኋት ከሚል የበሸሻ ጎረምሳ ጋር ሞታችንን፥ ቀብራችንን እናድርግ ከሚል ግብዝ፥ አደርባይና አስመሳይ ጋር መላፋት እንዴት ያደክማል?! በአጭሩ አያልቅበት አህመድ ከቱርክ በዜሮ ተመልሷል። ያጣው እንጂ ያገኘው አንዳች ነገር የለም። ዋርካ በጠፋባት ሀገር ብሳና በዝቶ እንዲህ መቀለጃ መሆናችን ቅስም ይሰብራል። ይህን ዘመን እንዲያሳጥረው በጸሎት እየተጋችሁ ያላችሁ በርቱ። ነፍጥ አንስታችሁ ዱር የገባችሁም ጊዜው ቀርቧልና ግፉበት። የውስጥ ትግል እያደረጋችሁ ያላችሁ ወገኖችም የጠቆረው ሰማይ ወገግ ሊል ተቃርቧልና ተስፋ እንዳትቆርጡ። በእርግጥ ሊነጋ ሲል የሚጨልም ሰማይ ከላያችን ላይ እንደእንቅብ ቢደፋብንም ይህን ዘመን መሻገራችን አይቀርም። አቶ ደመቀ አደራ! በአንጎል ለቀነጨረው የብልጽግናው መንደር ቅድሚያ ስጥና እነሱን ከደዌ፥ እኛንም ከመከራ ገላግለን።
49
7
130
9,946
I wrote the following words almost a year ago, under the title "Misinterpreted Promises and Deceptive Tactics: The Somaliland-Ethiopia MOU Fallout.” “The complete fruition of the agreement ( meaning the MOU) is yet to be witnessed, especially in light of the recent disclosure of deception surrounding the pact. In the aftermath, as the dust settled, what remained was a deceived and naive Somaliland president and a Prime Minister ( Abiy Ahmed) who, at least in this instance, attempted to deceive the public using a strategy of hoodwinking and obfuscation, gloating at his skill in the art of deception.” Read the following communique from Ankara, dated 12/12/2024. The fate of that MOU is sealed. It is dead and buried. Then you would realize that my words above were not based on idle speculation but an outcome of having a complete knowledge of the deceitful nature of Abiy Ahmed. @AbiyAhmedAli @FdreService @Mustafe_M_Omer @AlainAmharic @EthioReporter @ETHZema @MOJEthiopia @BilleneSeyoum @NeaminZeleke @PMEthiopia @BBCNews @dw_amharic @RedwanHussien @danielkibret @ethioNDC @VOAAmharic @fanatelevision @walta_info @ebczena @EmishawEskedar @HOAAffairs
1
40
6
80
9,174
የሶሪያው ግልገል አምባገነን በሺር አል አሳድ ዛሬ ተገረሰሰ። ሥልጣን ከአባቱ በመውርሱ ሀገሪቷ የቤተሰብ ርስት ስለመሰለቸው፣ ፕሬዝደንትነቱን የሙጥኝ ብሎ ሶሪያን ወደ አስከፊ የእርስበርስ ጦርነት ከተታት። ለ13 ዓመታት የዘለቀው ጦርነትም ሶሪያን የተለያዩ የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች መፋለሚያ አውድማ በማድረግ አደቀቃት፣ ሕዝቦቿም በሺዎች ሞተው፣ በሚሊዮኖች ደግሞ ተሰደው አለም ላይ ተበተኑ። በውጪ ኃይላት ድጋፍ ሥልጣኑን ተንጠልጥሎ ቢቆይም፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ነገሮች በቅጽበት ተቀያይረው አማጺያኑ ገስግሰው ደማስቆ ሲደርሱ “ሶሪያ ወይም ሞት” እያለ ሲፎክር የነበረው አሳድም እንደማንኛውም አምባገነን ፈረጠጠ። ለመሆኑ ለዓመታት ተከፈፍለው እና ተዳክመው የነበሩት የሶሪያ አማጺያን እንዴት በዚህ ፍጥነት ሥርዓቱን ሊገረስሱ ቻሉ? ለ13 ዓመታት የቆየው የእርስበርስ ጦርነት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አላሸቀው፤ የመንግስት አስተዳደራዊ መዋቅርን አወላለቀው። ሠራዊቱ እና ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች በውጪ መገዝገዝ እና ለውስጣዊ ክፍፍል በመዳረግ አቅማቸውን አሽመደመደው። አማጺያኑ የተከፋፈሉ ቢሆንም እንኳ፣ የተራዘመው የእርስበርስ ጦርነት የመንግስትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ የሥልጣን ምሰሶዎች ቀስ በቀስ በመገዝገዝ ሰባበራቸው። በሌላ አባባል አሳድ ፕሬዝደንትነቱን ተቆናጥጦ መቆየት ቢችልም፣ የሶሪያ ሀገረ-መንግስት አቅም ከቀን ወደ ቀን እየሞተ ነበር። አሳድ ግን አማጺያኑ የተከፋፈሉ በመሆናቸው እና ከውጪ ኃይሎች በሚያገኘው ድጋፍ በመተማመን፣ የሥልጣን ምሰሶውን መሽመድመድ አልተገነዘበም ነበርና እውነታን ተቀብሎ አቅሙን መልሶ ለመገንባት ከመሞከር ይልቅ እየተኮፈሰ ቀጠለ። በቅርቡ ግን ነፍስ አባት ሆነው ያቆዩት ኃይሎች በራሳቸው ጦርነት ተጠምደው ድጋፋቸውን መቀነሳቸውን የተረዱት አማጺያን የተቀናጀ ዘመቻ ሲከፍቱበት፤ የተሽመደመዱት የሥልጣን ምሰሶዎች በቅፅበት ወዳደቁ። አሳድ ከተጠናወተው አምባገነናዊ መኮፈስ ሲነቃ፣ እግሩ የወላለቀ የሥልጣን ወንበር ላይ መቀመጡ ታየው። ምንም ማድረግ አልቻለም። የሀገሪቷን የፖለቲካ ችግሮች በድርድር እና ውይይት ለመፍታት ሲቀርብለት የነበረውን ጥሪ ሁሉ በእብሪት እምቢ ብሎ፣ በሰላማዊ ሰልፍ መብቱን የጠየቀን ሕዝብ ላይ በጄት ቦምብ አዝንቦ፣ የእርስበርስ ጦርነትን አስነስቶ፣ ያቺን ስመጥር ታሪካዊ ሀገር በታትኖ በውርደት ፈረጠጠ። የሶሪያ ዜጎች በአሳድ መገርሰስ ቢደሰቱም፣ የፈራረሰችውን ሀገራቸውን መልሶ መገንባት ቀላል አይሆንላቸውም። ሀገሮቻቸውን በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ዘፈቀው በውጪ ህይሎች ነብስ አባትነት ስልጣን ላይ ተንጣልጥለው ያሉ ሌሎች ግልገል አምባገነኖች ከአሳድ ተምረው ሳይዘገይ ይታረሙ ይሆን? አይመስለኝም። አምባገነኖችን ከሚያመሳስላቸው ባህሪያት ውስጥ ዋነኛው፣ አንዱ ከሌላው አለመማር ነውና!
304
168
37
1,078
112,319
የሶሪያው አምባገነን የበሸር አል አሳድ ውድቅት፣ በአብይ ካምፕ ሸብር በፋኖ ቤት መነቃቃት ይፈጥራል። አሳድ ስብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በሰላም የጠይቁ ዜጎቹን፣ በጅምላ ጨፈጨፈ። ሰላማዊ መንገድ ዘግቶ ዜጎቹን ነፍጥ አንስተው እንዲታገሉት አደረገ። የውጭ መንግስታት የወታደርና የመሳሪያ ድጋፍ አግኝቶ የገዛ ህዝቡን በጄቶች በከባድ መሳሪያዎች ጨፈጨፈ። ይህ አልበቃ ብሎት የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅሞ ዜጎቹን ፈጃቸው። በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩት የሞትን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የመፈናቀልና የስደትን ጽዋ ተጎነጩ። ያች ጥንታዊ የሆነቸውን ሶሪያ የምትባል ሃገር አወደመ። ሶሪያን ወደ ድንጋይ ዘመን መልሶ፣ ዳምሰቀስ ዋና ከተማውን እያሰማማረ ንጉስ ነኝ ብሎ ቀጠለ። አሳድ ተቃዋሚዎቹን አሸባሪ እራሱን ህግ አስከባሪ አድርጎ አስቀመጠ። በእብሪት ተወጠረ። በጦርነት የሚያሸንፈኝ ወንድ አይኖርም ብሎ ደነፋ። የሰላማዊና ህጋዊ መድረኩን ለተቃዋሚዎች ዘግቶ፣ የውሸት ምርጫ እያካሄደ፣ “በምርጫ መጥቻለሁ በምርጫ አውርዱኝ” ብሎ ተሳለቀ። የሃገሪቱን ስልጣንና ሃብት በጥቂት ታማኞቹ እጅ አስገብቶ፣ ህዝብ ሲቀጠቅጥ የሃገር ሃብት ሲያዘርፍ ከረመ። ይህን እያደረገ የህዝብ ተቃዎሞ የገጠመውን አገዛዙን እየጠጋገነ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከማርች 15 2011 አመታት ጀመሮ ለ13 አመታት እየተንገዳገደ ሰነበተ። ሆኖም ግን ለፍትህና ለነጻነት ትግላቸውን የጀመሩት የሶሪያ ተቃዋሚዎች፣ ስህተታቸውን አርመው፣ በመሃከላቸው የነበረውን ልዩነት አስወግደው እንደገና በአንድነት ከአሳድ መንግስት ጋር ግፍጫ ውስጥ ሲገቡ የአሳድ መንግስት ለመፍረስ የፈጀበት ጊዜ አንድ ሳምንት ብቻ ሆነ። በትናንትናው እለት በኖቬምበር 7 2024 ወደቀ። አሳድ የገባበት ጉድጓድ አልታወቀም። ይህ ሃቅ "በዚህ ዘመን በጠመጃ ትግል መንግስት መቀየር አይቻልም። ለአንድ ሽህ አመታት ከስልጣኔ የሚነቀንቅኝ አይገኝም። በምርጫ መጥቻለሁ በምርጫ አሰውግዱኝ "እያለ፣ ልክ እንደ በሽር አላሳድ የገዛ ህዝቡን በጄትና በድሮን እየጨፈጨፈ፣ በከተማ ልማት ስም የአዲስ አበባን ህዝብ እያፈናቀለ አራት ኪሎ ላይ ተኮፍሶ ለተቀመጠው የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዛ ሸብር ፈጣሪ ነው። የሶሪያ ሃቅ በዚህ ዘመንም አገዛዞች በጠመንጃ ትግል መውደቅ እንደሚችሉ፣ የአብይ አህመድ ጽዋም ከበሸር አላሳድ የተለይ እንደማይሆን ያመላከተ ነው። የአብይ አህመድ በየአደባብዩና በየቢሮው የተሰቀሉ ምስሎቹ በህዝብ እየተቀደዱ እንደሚወድቁ፣ ጊዜ አግኝቶ ያሰራው ሃውልት ቢኖር እንደ በሺር አላሳድ ሃውልት በህዝብ እንደሚፈርስ ያሳዬ ሃቅ ነው። እብሪትና ጉራ፣ ድንቁርና እና ጥራዝ ነጠቅነት በህዝብ ቁጣ ፊት የትም እንደማያደርሱ፣ እዩኝ እዩኝ እንዳላሉ ሁሉ ደብቁኝ ደበቁኝ የሚባልበት ጊዜ መምጣቱ አይቀሬ መሆኑ የሚያሳይ ነው። ሌላው የሶሪያው ሃቅ በፋኖ ቤት መነቃቃት ፈጣሪ ነው። የሶሪያ ታጋዮች አሳድን የጣሉት፣ ከምንም ነገር በላይ በአንድነት ለመታገል በመወሰናቸው ነው። ፋኖዎች የራሳቸውን አንድነት በወጉ መልክ አስይዘው፣ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው ጋር በጋራ ለመታገል የቆረጡ እለት፣ የአብይ መንግስት እንደ በሽር አላሳድ ፣ በአፈሳ የመለመላቸው ወታደሮቹ አያዱንትም። ህዝብ የሚጨፈጭፍባቸው ድርኖችና ጄቶች እያተርፉትም።፣ እንደጋን ቦርጫቸው ያበጠው ጄነራሎችና በሆዳቸው የሰበሰባቸው አሸርጋዶቹ ጸሃይ እንደመታው ቅቤ ከመቅለጥ በስተቀር ከፊት ሆነው አይታደጉትም። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አብይ አህመድ የሚያዘነበው የመከራ ዝናብ አላቆም ያለው በአብይ ጥንካሬ ሳይሆን በምንቃወመው አካላት የአንድነት እጦት ብቻ ነው። አንድነት እንደሶሪያ ታጋዮች በሳምንት ሳይሆን በቀናት የአብይ አህመድ አገዛዝ መንቀያው ፍቱን መሳሪያ ነው። ይቻላል። @AbiyAhmedAli @FdreService @Mustafe_M_Omer @AlainAmharic @EthioReporter @ETHZema @MOJEthiopia @BilleneSeyoum @NeaminZeleke @PMEthiopia @BBCNews @dw_amharic @RedwanHussien @danielkibret @TayeAtske @ethioNDC @VOAAmharic @fanatelevision @walta_info @ebczena @EmishawEskedar @HOAAffairs
75
14
157
25,424
ሰበር ዜና በግዳጅ ታፍሰው ብር ሸለቆ ማሰልጠኛ የገቡትን በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የአማራ ፋኖ በጎጃም በወሰደው ኦፕሬሽን ካምፑን ሰብሮ አስወጥቷቸዋል። ማሰልጠኛ ካምፑን የማይጠብቅ ሠራዊት አገር ሲጠብቅ አስበኸዋል?😂 ደስ ደስ እያለኝ ነው 😂😂
14
46
3
175
7,785
It has been over six months since the assassination of Batte Urgessa. Yet, to this day, justice remains elusive. The @EthioHRC is said to have completed its investigation into his murder, but inexplicably, the findings remain withheld from the public. This lack of transparency is a glaring failure of accountability. Batte’s assassination was a heinous act of violence that demanded immediate and thorough accountability. While the EHRC initially pledged to uncover the truth, its inability or refusal to release the investigation report long after its completion raises critical questions: What is being hidden? Who benefits from this silence? The consequences of this failure are far-reaching. Batte’s family now live in exile in the United States, forced to flee Ethiopia due to fear for their safety. Their exile is a tragic testament to the government’s unwillingness to protect its citizens. It also underscores a pattern of impunity we have seen over the last six years. The withholding of the EHRC’s report also represents a broader systemic issue in Ethiopia. When justice is delayed, withheld, or denied, it creates a vacuum where impunity thrives. This is not just about Batte Urgessa—it is about the integrity of Ethiopia’s institutions and their commitment to accountability. Justice for Batte Urgessa is not just about seeking accountability for one man’s murder—it is about setting a precedent that no life is expendable, no family’s suffering is ignored, and no voice for justice can be silenced. It is time for the EHRC to fulfill its mandate. Release the report. Deliver justice. End the impunity. For Batte Urgessa, his family, and the countless others who have been denied their fundamental rights, the world is watching—and history will remember.
161
224
26
945
84,355
በስብዕና መዛባትና የአእምሮ ህመም ተጠቂው አብይ አህመድ
84
7
171
14,018
መደመጥ፣ ተደጋግሞ መደመጥ ያለበት ቃለምልልስ ሰዉየውን፣ ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰንን፣ ልትወደው ወይም ልትጠላው ትችላለህ። የአፍሪካን እና የቀንዱን ፖለቲካዊ ሁኔታ እየበለተ፣ እየሰነጠቀ እየበታተነ የሚያቀርብበትን ከፍተኛ ብቃት፣ አቅምና ልምድ ለአንድ ደቂቃም ቢሆን መጠራጠር ግን አትችልም። የቀጠናዉን ሁኔታ በሚገባ ከተነተነ በሗላ በኢትዮጵያዊዉ ከማል አታቱርክ (አብይ አህመድ) የምትመራው ኢትዮጵያ በሁሉም መሰኩ የገባችበት አጣብቂኝ ሃገሪቱን ለከፍተኛ የደህንነት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ኪሳራ እንደዳረጋት ያብራራል። ካነሳቸው ጉዳዮች መሃል ድንቁርና እና እብሪት ያሳበጠው፣ አጎብዳጆቸ ያደለቡት አቅሙን ማወቅ የተሳነው ኢትዮጵያዊው ከማል አታቱርክ በዲፕሎማሲው መሰክ በሃገሪቱ ላይ ያደረሰውን አሳሳቢ ኪሳራ መሃመድ ሃሰን ያብራራበት መንገድ ማንም ሃገሩን ከምር የሚወድ ዜጋ ማስደንገጡ አይቀርም። እደል አግኝታችሁ ቃለ መጠይቁን ባታዳምጡ የምትጎዱት እራሳችሁን እንጂ መሃመድ ሃሰን አይሆንም። እሱ ያለውን ኣበርክቷልና ንፉግ አይባልም። ቃለ መጠይቁን እንድታዳምጡ ለማበረታት መሃመድ ሃሰን አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ ጥልቁ ከማይታወቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደጨመረው የሰጠውን አስተያየት ጨመቅ አድርጌ ላቅርብላችሁ። ቃል በቃል አይደልም የጨመቅሁት ። መሃመድ እንዲህ ይለናል። ለፓርኮች፣ ለሎጆችችና ለኮሪደር ልማት የሚያጠፋወን ገንዘብ ለማግኘትና ሰልጣኑን በጉልበት ለማሰጠበቅ የሚሻውን የጦር መሳሪያ ለመቃረም ሲል፣ አብይ አህመድ፣ ኢትዮጵያን የሚያክል ትልቅ አገር አረብ ኤመሬት የምትባል ትንሸ ሃገር ጫማ ስር እንድትወድቅ አደረገ። ኤመሬት ደግሞ” ይላል መሃመድ ሃሰን ከህንድ ውቂያኖስ አንስታ፣ በአረቢያ ገልፍና በቀይ ባህር ላይ አቋርጣ እስከ ሜድትራኒያ ባህር ድረስ በየባህሩ ዳርቻዎች የሚገኙ የሌኦችን ሃገሮ ወደቦችን ሁሉ የመቆጣጠር ስትራተጂ ቀይሳ የተነሳች ሃገር ናት ። ለአብይ የሰጠችው የገንዘብና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይህን ፍላጎቷን ለማስፈጸም በሎሌነት ልትጠቀምበት እንደምትችል አውቃ ነው። የሆነውም ይህ ነው። በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መሃከል አለምን ያስጮኸውና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ስም ወደብ እናገኘን በሚል ምክንያት ለሶማሌላንድ ሃገራዊ እውቅና ለመስጠት የመግባባቢያ ሰንድ እንዲፈረም ያደረገችው ኤመሬት ናት። የመግባቢያ ሰነዱን መዘዝ መሃመድ እንዲህ ያብራራዋል። የመግባቢያ ሰነዱ በመፈረሙ መላው የአለም ሃገራት፣ የሩቅና የቅርብ ሃገራትን ጨምሮ፣ ሃብታምና ደሃ፤ የቀኝ ሆነ የግራ ርእዮት የሚከተሉ ሃገራትን አካቶ፣ የተባበብሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ህብረት ሌሎችም አለም አቀፍ ድርጅቶች ታክለውበት “ኢትዮጵያን አይንሸ ላፈር” ያሉበት ሁኔታ ፈጠሮ እንደነበር ይታወቃል። አብይ አህመድ ግን በኤመሬቶች አደፋፋሪነት ይህን የአለምቀፍ ማህበረሰብ ውግዘት ከቁም ነገር ባልቆጠረ መልኩ በጀመርኩበት እገፋለሁ ቢልም መዘዙ የዋዛ እንዳልሆነ ስለገባው እግሩን ሲጎትት ውሉን በተግባር ሳይተረጉም እስካለንበት ወቅት ደርሶ ነበር። ይሁንና በዚህ ጉዳይ ከማል አታቱርክንም ሆነ ኢትዮጵያን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ የጨመረው ጉዳይ የተከሰተው ከሩቅ ሳይሆን በራሱ በሶማሊያላንድ ውስጥ ሆኖ አረፈው። የመግባቢያ ሰነዱን በሱማሌላንድ በኩል የፈረመው የኤመረቶቹ ፈረስ፣ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እራሱ በጠራው ሃገረዊ ምርጫ እንዳይሆኑ ሆኖ በተፎካካሪው አብዲራህማን መሃመድ አብዱላሂ ተሸነፈ። አዲሱ የሶማሌላንድ ፕሬዚደንት የመግባቢያ ሰነዱን ቀዶ የሚጥል መሆኑ ፍንጮች አስቀድመው ታይተዋል። ይህ ሲሆን አብይ አህመድ መካሪ አጥቶ ኢትዮጵያን ለብዙ ዳፋ የዳረጋትን ውሳኔ ወስኖ የገባብት ጉዳይ ውሃ በላው ማለት ነው። የመግባቢያ ስምምነቱ፣ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከሶማሊያ እንዲወጣ፣ ግብጽ በሱማሊያ ሰላም አስከባሪ የምታስገባበትን፣ ሶማሊያን መሳሪያ የምታስጣቅበትን፣ የጦር ሃይሏን ስልጠና የምትሰጥበትን ሆኔታ ፈጥሮላታል። ግብጽና ቱርክ የሶማሊያን የባህር ዳርቻዎች የሚቆጣጠሩበትን እድል አመቻቸላቸው። በኤርትራ በግብጽና በሶማሊያ መሃከል ባለፈው ወር አስመራ ላይ የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ዋናው ማእከል ያደረገው የሃገሮችን ሉአላዊንት ለማስከበር በጋር መቆምን እንዲሆን ያደረገው ኢትዮጵያ የሱማሌያ ሉአላዊነት መጋፋቷና ሌሎችንም በዙሪያ ያሉ ሃገሮችን የባህር በር በጉልበት እናገኛለን የሚል ማስፈራራያዋ ሆነ። ከሱማሌ ላንድ የመግባቢያ ሰነድ ኢትዮጵያ ውደብ አላተረፈችም። ማስፈራሪያዋም ያሁኑ ትውልድ ሳይሆን መጪው ትውልድ በተግባር የሚተረጉመው ነው ተብሎ ተናጋሪዎቹ ፍከራውን ትተው መሸሽ ጀመሩ። ኢትዮጵያ ያተረፈችው ውርደት፣ አለም አቀፍ ቁጣ፣ በቀጠናው ሃገራት በጥርጣሪ እንድትታይና የቀጠናው ሃገራት አጉራ ዘለልነቷን በጋራ ለመመከት እንዲሰባሰቡ ማድረግ ብቻ ነው። መሃመድ ሃሰን ሌላውን ኢትዮጵያን ትልቅ ችግር ውስጥ የደፈቃትን ጉዳይ እንዲህ ይገጸዋል። ሌላው በኤመሬቶች ጉትጎታ ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ የጣላት ጉዳይ የሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ነው። ኢትዮጵያ የኤመሬት መንግስት የሚደገፈውን የሱዳንን ህጋዊ መንግስት የሚዋጋወን በጄነራል ደጋሎ የሚመራውን የፈጥኖ ደራሽ ቡድን ደጋፊ ሆና፣ መሳሪያ፣ ስነቅና መድሃኒት ከኤመሬቶች እየተቀበለች አስተላላፊ ሆነች። አሁን ሱዳን ውስጥ የሚታየው ሁኔታ፣ ግብጽ አምራ የሱዳንን መንግስት በመደገፏና የሱዳን መንግስትም በሚገባ ተደራጅቶች መዋጋት በመጀመሩ የፈጥኖ ደራሹ ሃይል እንዳሰበው ሱዳን መቆጣጠር ቀርቶበት ተጠቃሎ ሊሸነፍ የሚችል መሆኑ ነው። የሱዳን ህጋዊ መንግስት በህጋዊነቱ በአለም ላይ ብዙ ድጋፍ አለው። አንድን መንግስት በሃይል ለመጣል የሚደረግን ሙከራ አለም የሚደግፈው ስላልሆነ። ኢትዮጵያ የኤመሬቶች ተላላኪ በመሆን በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ገብታ ማቡካቷ በተፋላሚዎቹ ወገኖች ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ የልብ ወዳጃችን ናት በሚለው የሱዳን ህዝብ ስሜት ላይ ትልቅ ጉዳት አድርሷል። የአልቡርሃን መንግስትና የሱዳን ህዝብ ኢትዮጵያን በጠላትን እንዲያዩና ሱዳን ኢትዮጵያን በስጋት ደረጃ ከሚያዩት የቀጠናው ሃገሮች ጋር አሰላለፏን አሳምራ፣ ግብጽ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ በፈጠሩት ህብረት ውስጥ መግባቷ የማይቀር ነው። በተለይ የትራምፕ መመረጥ የአልቡረሃን መንግስት በግብጽ አማካይነት የአሜሪካንን ሙሉ ድጋፍ የሚያገኝ እንደሚሆን መጠራጠር አይቻልም። የኢትዮጵያ ከማል አታቱርክ እብሪት ካስደነበራቸው ሃገሮች ጂቡቲ አንዷ መሆኗ ይታወቃል። ጅብቲም ብትሆን አሰላለፏን ክሱዳን ከሱማሌያ ከኤርትራና ከግብጽ ጋር የማታደርግበት ሁኔታ የለም። የዲፕሎማሲ ኪሳራ ማለት ይህ ነው። በኢትዮጵያ ላይ ሌላው ኪሳራ የሚመጣው ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሆኖ ከመምጣቱ ጋር የተያያዘ ነው። ትራምፕ ከግብጽ፣ በተለይ ከመሪው ከአልሲሲ ጋር ያለው በጣም የቀረበ ወዳጅነት ይታወቃል። መሃመድ ሃሰን ባይጠቅሰውም የግብጽ የደህንነት መስሪያ ቤት ከባይደን ጋር ትራምፕ ላደረገው የመርጫ ውድድር 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እዳደረገ በመረጃ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ዶላንድ ትራምፕ የግብጾችን ፍላጎት በቅድሚያ ከሌሎች የአካካቢ ሃገሮች አስቀድሞ ለሟሟላት እንደሚንቀሳቀስ ግልጽ ነው። ትራምፕ በግብጽ በኩል የሚቀርብለትን ጥያቄ እየተከተል በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያስድር ውሳኔ እንደሚወስን አንጠራጠር። ትራምፕ ከዚህ በፊትም በግልጽ ውግንናውን አሳይቷል። የአሜሪካ ምርጫ ግብጽ በአሜሪካ ውስጥ ተደማጭነቷ እንዲጎላ ያደረገ ሁኔታ ተፈጠሯል። የትራምፕ መመረጥ፣ በተለይ የአሜሪካ ዴምክራቲክ ፓርቲ የቀጠናው ተላላኪ በመሆን፣ ከዴሞክራቲክ ፓርቲ ባላስልጣናት ጋር በሙስና ጭምር ተሳስሮ ትልቅ ድጋፍ ሲያገኝ የነበረውን ወያኔ አየር ላይ የሚያንሳፍፍ ይሆናል። ወያኔና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ባላስልጣናት በጋራ እያሴሩ አበሳዋን ሲያሳዩዋት የነበረችው ኤርትራ ፋታ የምታገኝበት ሁኔታ ይፈጠራል። አልሲሲ አሜርካን እና ኤርትራን ለማቀራረብ የሚችል መልካም አጋጣሚ ተፈጥሮላቸዋል። መሃመድ ሃሰን ባይለውም ፣ እኔ ከማውቀው ተነስቼ በዴሞክራቶች ደጋፊነት የኢሳይስን መንግስት መጣል እንችላለን በሚል ስሌት በማንኛውም መመዘኛ ከየትኛውም ሃገርና ህዝብ በላይ በከፈተኛ ወዳጅነት ተቀራርቦ መስራት ከሚገባው ከኤርትራ መንግስታና ህዝብ ጋር መቃቃርን የመረጠው የኢትዮጵያው ከማል አታቱርክ አገዛዝ ትልቁ የዲፕሎማሲ ክሽፈቱ መሆኑ እየታየ ነው። እንግዲህ ድንቁርና በወለደው ድፍረት በሚመራ መሪ የተነሳ እንዲህ አይነት የዲፕሎማሲ አጣብቂኝ ውስጥ የወደቀችው ኢትዮጵያ ውስጣዊ አንድነቷ የጠበቀ፣ ኢኮኖሚያዋ የተረጋጋ፣ ፖለቲካዋ የስከነ ቢሆን ኖሮ የመጣውን የዲፕሎማሲ ወጀብና ሃገራዊ መዘዙን መቋቋም ትችል ነበር። የኢትዮጵያ ሁኔታ ግን የከማል አታቱርክን የፕሮፓጋንዳ ጩኽት ወደጎን አድረገን ካየነው የዚህ ተቃራኒ ነው። የደህንነትና የመካለካያ ተቋሟ ከጉራ በስተቀር በተንኮታኮተበት ተንኮታኩትዋል። ኢኮኖሚዋ ደቋል። ፖለቲካ መስከን አቅቶት በአራቱም መአዘን ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ስርአቱን በሚገዳደሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል።በተለይ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በመሆን ህልውናዋን በማንበር ከፍተኛ መስዋእትነት ለዝንተ አለም ሲከፈል የኖረው የአማራ ህዝብ ህልወናውን ለማስከበር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገና የአብይን ሰራዊት ባሽመደመደበት ሁኔታ የመጣ የዲፕሎማሲ ውድቀት ለሃገራችን ኢትዮጵያ ለህዝቧ ከልብ እንድንሰጋላት የሚያደርግ ነው። ይህን ሃቅ ሚሊየን የብልጽግና የዲጅታል ሰራዊት በማሰለፍ መሸፈን፣ ሽዎች ዩትበሮችን በመክፍል ማድስበስበ፣ እልፍ አደግድጊዎችን አሰባስቦ፣ አንዴ ናፖሊዮን፣ አንዴ ከማል አታቱርክ፣ አንዴ ሙሴ፣ አንዴ ባለራእዩ መሪ፣ ብለው እንዲዘመሩ በማድረግ ብን ብሎ እንዲጠፋ ማድረግ አትችልም። ሃሳቡን በሃሳብ ላይ እየደርደረ፣ እንደግብጽ ፒራሚድ ያቆመውን መሃመድ ሃሰን በሃሳብ ከመሞገት ይልቅ በስድብ መዝመትም የሚያመጣው ፋይዳ የለም። አቅም ያለው የመንግስት ሚኒስቴር ወይም ቃል አቀባይ እያንዳንዷን ነጥብ እያነሳ ውድቅ ሲያደርጋት እንይ። መሃመድ ሃሰን መርዶ ነጋሪ ብቻ አይደለም። ወደ መርዶ የሚውስደው መንገድ እንዴት ማስቆም ይቻላል የሚል ጉዳይ ላይ ይናገራል። በተለይ የኢትዮጵያ ባላስልጣናትና አጃቢዎቻቸው፣ ከዛም ሁሉም ሃገሩን የሚወድ ዜጋ ያዳምጠው እላለሁ። አድምጣችሁ ያላዳመጡ እንድያዳምጡ አድርጉ! youtube.com/live/qXUUXBwciuE… @AbiyAhmedAli @FdreService @Mustafe_M_Omer @AlainAmharic @EthioReporter @ETHZema @MOJEthiopia @BilleneSeyoum @NeaminZeleke @PMEthiopia @BBCNews @dw_amharic @RedwanHussien @danielkibret @TayeAtske @ethioNDC @VOAAmharic @fanatelevision @walta_info @ebczena @EmishawEskedar @HOAAffairs
64
4
112
13,152
ክብር በሐገር ቤት ከፍተኛ ስቃይና በጦርነት ላይ ላለው ወገናችሁ በዚህ መልኩ ድምጽ ላሰማችሁ ዳያስፖራዎች!! 🙏
10
232
4
389
10,887
The Amhara people are being slaughtered while the world looks away. It’s time for the #AmharaDiaspora to act—raise your voices in rallies, demand accountability, and shout for those who can't. #WaronAmhara #StopAmharaGenocide @USEmbassyAddis @UKinEthiopia @AsstSecStateAF @eu_eeas
4
185
5
138
3,344